በዝርዝር

የወሻኖ ወሎ ዋሻ

የቱሪስት መስህቡ አይነት፡ : ተፈጥሯዊ

የቱሪስት መስህቡ ያለበት ቦታ፡: በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ ወሻኖ ቀበሌ

በዝርዝር

አልቾ ውሪሮ ወረዳ የብዙ ታሪካዊ፣ ሠው ሠራሽና የተፈጥሮ የቱሪስት መስህብ ባለቤት ናት፡፡ ይሁንና እነዚህን መስህቦቿን አልምታም ይሁን አስተዋውቃ ተጠቃሚ የሆነች አይደለም፡፡ ከነዚህም ውስጥ የወሻኖ ወሎ ዋሻን ብንመለከት፡- የወሻኖ ወሎ ዋሻ በወረዳችን ከሚገኙ የቱሪስት መስህብ ቦታዎች አንዱ ነው፡፡ የወሻኖ ወሎ ዋሻ የሚገኘው ፉቻሬ ቀበሌ ድንበር በወሻኖ ቀበሌ ውስጥ ከቃዋቆቶ 5ኪ/ሜ ገደማ በስተ ምዕራብ ሰሜን ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ መስህቡንም ለመድረስ በየትኛውም የመጓጓዣ ዓይነት ቦታው ድረስ መድረስ ይቻላል፡፡ ይህን ዋሻ መቼና በምን እንደተሠራ በእርግጠኝነት የሚናገር አልተገኘም ነገር ግን ለምንና ማን ይጠቀሙት እንደነበር ግን የሚናገሩት ታሪክ አዋቂ ሽማግሌዎች ይህ ዋሻ በተለይም በሚሊሊክ ጦርነት ጊዜ እንደሚታወቀው ትልቅ ተቃውሞ የገጠመው አንዱ በስልጤ አባቶች ነበር በዚያን ጊዜ ይህ ዋሻ ትልቅ ምሽግ ሆኖ በጉራጌ በኩል የሚመጣውን ጦር ሲፋለሙ መጠለያ በመሆን ትልቅ ባለ ኡለታ መሆኑን ሽማግሌዎቹ ይናገራሉ፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላም በጣሊያን ወር ጊዜም ቢሆን ትልቅ ፋይዳ እንደነበረው ይናገራል፡፡ አሁንም ቢሆን በድሮ ይዘቱ ባይኖርም ዋሻው በጣም ሰፊና ማራኪ አሠራር የሚታይበት ነው፡፡ የመጀመሪያ ቅርጹን ሲናገሩ መሃል አካባቢ በጣም ትንሽ ቀዳዳ እንደነበረውና መውጫና መግቢያው ከተለያየ ቦታ እንደነበረ ነው፡፡ መሀል አካባቢ የተሠራችው ቀዳዳ ለጪስ መውጫና ምግብ ሲያልቅባቸው የሚቀበሉበት እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ዋሻ አጠገብ ወንዝ ስላለ ምግባቸውን እዛው ሆነው በቀላሉ ማብሰል ይችሉ እንደነበረም ይናገራል፡፡ አሁን ግን መሀል አካባቢ ያለችው ቀዳዳ በአካባቢው ሰዎች አማካኝነት እንደሰፋች ይናገራሉ፡፡ ዋሻው አሁን ባለው ይዘት ያለምንም ችግር እስከ 10 ሜ ድረስ የሚያስገባ ቢሆን ነገር ግን በተለያዩ ማዕዘናት በጣም ጠባብና የሚያስፈሩ መንገዶች ይታያሉ፡፡ ነገር ግን የወሻኖ ታሪክ ስንሰማ በጣም ረዥምና እስከ ሙጎም ይደርስ እንደነበር ታሪክ አዋቂ ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ በዋሻው አሁን ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ አንዲት እናት በዋሻው የድሮ ብርና ጌጦች ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ዋሻ ውስጥ ገብተው እንዳስቆፈሩና በውስጥም የተለያዩ ባህላዊ ዕቃዎችን አካፋ እንዳገኙ ማየታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ዋሻውን እስከ ቅርብ ጊዜ የዱር እንሰሳት ይጠቀሙት ስለነበር በአካባቢው ሰዎች ችግር ሲፈጥሩ እነሱን ለማጥፋት በሚል ድንገት ከውጭ አምጥተው እንደጨመሩበትና ድንገት አሁንም እንዳለ ለማወቅ ችለናል፡፡ ስለዚህ ይህን አስገራሚ ዋሻ አሁን ካለበት አሳሳቢ ሁኔታ ለመታደግ ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ እያልን በሌላ ሰፋ ያለ ጥናታዊ ጹሁፍ እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት፡፡

<

© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved