በዝርዝር

ኤጎ ትክል ድንጋይ

የቱሪስት መስህቡ አይነት፡ : ተፈጥሯዊ

የቱሪስት መስህቡ ያለበት ቦታ፡: በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ ጉግሶ ቀበሌ በኤጎ መንደር

በዝርዝር

ኤጎ ትክል ድንጋይ ትክል ድንጋይ የሚገኘው በጉግሶ ቀበሌ በኤጎ መንደር ነው፡፡ትክል ድንጋዩ የወረደው መአከል ከሆነችው ቃዋቆቶ ከተማ በ18 ኪ.ሜ ከዞኑ ዋና ከተማ በ36 ኪ.ሜ ነው፡፡በዚ አከበቢ የተለያዩ ትክል ድንጋዮች ያሉ ሲሆን ይህ ትክል ድንጋይ ከሌሎች የሚለየው ቁማቱ 2.3 ሜ መሆኑ ነው ይሁን እንጂ የሰው ልጅ ቅርፅ የሆኑት አይን አፍ፣አፍንጫ፣ጡት እንዳሌሎች ትክል ድንጋዮች የሉትም ፡፡ሚነበቡ ጹሁፎችም እምብዛም አይታይበትም ለንጉሶች ድምበር ተተክሎዋል መባሉ ለአህመድ ግራኝ ፈረስ ማሰሪያ መገልገሉ ከሌሎች ያመሳስለዋል ፡፡ሌላው ደሞ ለየት የሚያረገው እስካሁን ከተገኙት ወይም ከተጠኑት ጣሊያን ኢትዮጵየን በወረረበት ግዜ በያረፈበት ቦታ እንደተከለውም ይነገራል ይህ ሊባል ያስቻለው በአብዛኛው በዐመት ዐመት ፀሀይና ዝናብ ብርድ ቢፈራረቅበትም እንኳን ለመፍረስ ለማርጀት አለመሰቡ ነው ፡፡በአጭሩ ኤጎ ትክል ድንጋይ በጥንት ግዜ በኣከበቢ ላይ ይኖሩ የነበረውን ማህበረሰብ ስነ-ቅርፅና ስነ-ጥበብ የሚያንፀባርቅበት ትክል ድንጋይ ነው፡፡ አጥኚዎች(ጎብኚዎች) ብዙም ሳይቸገሩ ከቡታጅራ---ወልቂጤ በሚወስደው መንገድ ወደ ቀኝ ታጥፈው 3 ኪ.ሜ ባልበለጠ ጉዞ ይህን ትክል ድንጋይ ማየት የሚችሉበት አጋጣሚ በመሆኑ የሰው ዘርን የስነ-ጥበብ ውጤቶች ቁልጭ ባለ ሁኔታ ተረድተው ይመለሳሉ፡፡

<

© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved