የቱሪስት መስህቡ አይነት፡ : አይታወቅም
የቱሪስት መስህቡ ያለበት ቦታ፡: በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ በቡኔ ሳቀሞና በቀጨሞ ቀበሌ ገበሬ ማህበር
ወረዳችን አልቾ ውሪሮ ወረዳ የብዙ ታሪካዊ ፣ ሰው ሰራሽ ፣ ተፈጥሯዊ መስህቦች በብዛት የሚገኙበት ወረዳ ናት፡፡ ከነዚህም ውስጥ የደንቃ ድልድይ አንዱ ነው፡፡ የደንቃ ድልድይ የሚገኘው በቡኔ ሳቀሞና በቀጨሞ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በአብጀት ትምህርት ቤት በቅርብ ርቀት በስተ-ደቡብ ይገኛል፡፡ ይህቺ ድልድይ አንድ ወጥ ድልድይ ሆኖ ወረዳችን ውስጥ ካሉት ትልቅ ወንዞች መካከል አንዱ በሆነው ኤዶ ወንዝ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ይህቺን ድልድይ በተፈጥሮም ይሁን ሰው ሰራሽ እንደተሰራች የሚያረጋግጥ መረጃ የለም ድልድዩ 1.50 ሜትር ስፋትና 3 ሜትር ርዝመት አሉት፡፡ የኤዶ ትልቁ ወንዝም ጤና ይስጥልኝ ብሎ ከስሯ ነው ሽሉክ የሚለው፡፡ የድልድዩ ርቀትን ስንመለከት ከቃዋቆቶ ከተማ 8 ኪ.ሜ ከወራቤ 20 ኪ.ሜ ርቀት አካባቢ ከወረዳው በስተ-ደቡብ ከዞን ደግሞ በስተ-ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ ይገኛል፡፡ ይህቺ መስህብ በተለይ ክረምት ወራት ላይ ኤዶ ወንዝ በከፍተኛ ደረጃ ሲሞላ ሁሉም ዞሮ ወደሷ መምጣት ግድ ስለሚለው ለአካባቢውና ለሩቅ መንገደኞች ትልቅ ባለውለታ ናት፡፡ ደንቃ ድልድይ ያለችበት አካባቢ በብዙ ሀገር በቀል ዛፎችና አቀበቶች የታደለ አካባቢ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ሀብቶቻችንን ተንከባክበን ወደ ልማት ለመለወጥ የሁላችንም ርብርብ ይጠይቃል፡፡
© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved
By logging in you agree to our Terms and Conditions and Privacy Policy