በዝርዝር

የገን ስልጤ መታሰቢያ መስጅድና መካነ መቃብር

የቱሪስት መስህቡ አይነት፡ : ሐይማኖታዊ

የቱሪስት መስህቡ ያለበት ቦታ፡: በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ ወዚር-1 ቀበሌ

በዝርዝር

የገን ስልጤ መታሰቢያ መስጅድና መካነ መቃብር በወረዳችን ከሚገኙ በርካታ ታሪካዊ ቅርሶች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ የዚህ ቅርስ መገኛ ስፍራ ልዩ ስሙ እራስ ጥበብ የሚባል ቦታ ሲሆን እራስ ጥብ በወዚር-1 ቀበሌ ገ/ማህበር ኑጌ ፎጥ ውስጥ ይገኛል፡፡ ከቃዋቆቶ ወደ ኩተሬ በሚወስደው መንገድ ላይ ከጣይሴ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት ወደ ምስራቅ አቅጣጫ በሚገኘው የእማር መንገድ የአንድ ሰዓት መንገድ ነው፡፡ መስጅዱና መካነ መቃብር የሚገኙበት ስፍራ በዝናብና በዙሪያው በሚገኙ ትንሽ ወንዝ የተሸረሸረ ከሚመስለው አካባቢ ወጣ ብሎ ተገንጥሎ ይታያል፡፡ ትንሽ ኮረብታማ ይመስላል፡፡ በስራው ላይ በመቆም በርካታ ነገሮችን በዙሪያው መመልከት ይቻላል፡፡ ገን ስልጤ በስልጤ ብሔረሰብ አፈ ታሪክ ውስጥ የብሔረሰቡ አባት ተብለው ከሚታወቁት ሀጂ አሊዬ ከሶስት ሚስታቸው ከወለዷቸው ስድስት ልጆች አንዱ ሲሆን እሱም በአሁኑ ወቅት በስልጢ በላንፎሮና በከፊል ዳሎቻና አልቾ ውሪሮ ወረዳዎች ለሚገኙ በርካታ ጎሳዎች የዘር ግንድ ምንጭ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ በተጨማሪም ሀጂ አልዬ ወደ አካባቢው ከመጡ በኃላ የገነቡትን ባህላዊ አስተዳደር ስልጣን ወራሽ እንደነበሩም የሀገር ሽማግሌዎች ያስረዳሉ፡፡

<

© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved