በዝርዝር

የጠረጋ ሸለቆና ንፋሱ

የቱሪስት መስህቡ አይነት፡ : ተፈጥሯዊ

የቱሪስት መስህቡ ያለበት ቦታ፡: በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ ጉግሶ ቀበሌ

በዝርዝር

የጠረጋ ሸለቆና ንፋሱ የሚገኘው በስልጤ ዞን በአልቾ ውሪሮ ወረዳ ከወራቤ በስተሰሜን አቅጣጫ በጉግሶ ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡ የሸለቆውን ርቀት ስንመለከት ከሀዋሳ 243 ኪ/ሜ ከዞን ዋና ከተማ ወራቤ 43 ኪ/ሜ እና ከወረዳው ዋና ከተማ 15 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይህን መስህብ ከሌሎች ለየት የሚያደርገው ተራሮች አናት ላይ ከፍተኛ የሆነ የንፋስ ኃይል መኖሩና ዓመቱን ሙሉ አረንጓዴ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ ምናልባትም ጥናት ቢደረግበት ሀገራችን ለተያያዘችው የኃይል ማመንጫ መሆን የሚችል የንፋስ ኃይል ያለው ነው፡፡ ተራሮቹ አናት ላይ ከባድ ንፋስ ስላለ መኖሪያ ቤቶችን ማግኘት ይከብዳል ከዚህም የተነሳ መኖሪያ ቤቶች በሸለቆው ውስጥ ባህላዊ ይዘታቸው ይዘው ይገኛሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ነው የአካባቢው ልዩ መጠሪያ ሹሉኬ ተብሎ የሚጠራው በሸለቆው ውስጥ አሞራዎች ይዘወተራሉ የአጥንት ሰበራም ያከናውኑበታል፡፡ ይህንም ልዩ ቦታ አምቦሰባር በመባል ይጠራል፡፡ መስህቡን ለመድረስ በተሽከርካሪ፣ በእንሰሳት ጀርባና በእግር መድረስ ይቻላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሸለቆው አካባቢ ቁጭ ብለው ቡታጅራን ከማየትም በተጨማሪ የተለያዩ የተፈጥሮ አጀቦችን መመልከት ይቻላል፡፡

<

© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved