በስልጤ ዞን አ/ው/ወ የአገታ ኤጀሬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የግንባታ ሂደት ላይ የአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ ያሳለፋቸው ሂደቶች የሚያሳይ ተሞክሮ

1.የአገታ ነባራዊ ገጽታ

የአገታ ቀበሌ ገ/ማህበር በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ ከሚገኙ ቀበሌዎች አንዷ ስትሆን መገኛዋ ፦

 በሰሜን ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ

 በደቡብ ስልጤ ወረዳ (አድበር ወለያ ቀበሌ)

 በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ<

 በስተ ምዕራብ ወሻኖ እና ጉግሶ ቀበሌዎች ያዋስኗታል

 የአገታ ቀበሌ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ በውሪብ እና በእንስላስ ታላላቅ ሰንሰለታማ ተራራዎች የታጠረች የገበቴ ቅርጽ የያዘች ፕላቶማ ገጽታ የላት ቀበሌ ናት።

 የቀበለው የመሬት አቀማመጥ ለመሰረተ ልማት ምቹ ባለመሆኑ ማህበረሰቡ ለከፍተኛ ስቃይና እንግልት ተዳርጓል።

2.የአገታ ከፊል ገጽታ በምስል


የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ፍለጋ ህጻነት እና ሴቶች ዳገት ቁልቁለቱን ߹ወንዘና ጫካውን አቋርጠው ጥዋት እና ማታ ከጅብ ጋራ በመጋፋት አጎራባች ወረዳዎች ደርሶ መልስ ተመላልሰዋል

ቡታጅራ߹ ስልጢ ወረዳና ቃወቆቶ በመመላለስ ጉልበታቸው ተበዝብዟል

ተስፋ የተጣለባቸው ትውልዶች ያለ ውጤት ባክነዋል

ሴቶች ተደፍረዋል߹ህጻናት ጉልበታቸው በመንገድ ተበዝብዟል

ሴቶች ለአካላዊ እና ለስነ ልቦናዊ ጥቃቶች ተዳርገዋል

ሀገር ተረካቢ ትውልድ ከመማር ይልቅ ወደ ከተማ ፈልሷል

በተገባልን ቃል መሰረት መስከረም 23/2013 የአገታ ኤጀሬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመሰረተ ድንጋይ ተጣለ



የአገታ ኤጀሬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዲዛይን ሂደት በፎቶ


የዋጋ ጥናቱን መሰረት በማድረግ እያንዳንዳቸው አራት የመማሪያ ክፍሎችን የሚይዙ 2ብሎኮችን ለመስራት በሚያስችል ሁኔታ በአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ የምህንድስና ክፍል ተጠንቶ ህዳር 2013 ግንባታ በይፋ ተጀመረ

የግንባታው ሂደት እና ክትትል

ዲዛይን እና የዋጋ ጥናት በአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ ኢንጅነሮች ግንባታው እስኪጠናቀቅ በየ ሳምንቱ የአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ ኢንጂነሮች ከሙያ እገዛቸው በተጨማሪ በራሳቸው ወጪ እየተመላለሱ ከፍተኛ ወጭ በመቀነስ በጥራትና በፍጥነት እንዲሰራ የአንበሳውን ድርሻ ሸፍነዋል፡፡ ግንባታው ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ማቴሪያሎች ነው የተጠናቀቀው ለአብነት ያህል ጣሪያውን ከፍተኛ ጥራት ባለው በኤጋሺት ኮርኒሱን በጂፕሰም ቦርድ ወለሉን ከፍተኛ ጥራት ባለው ሴራሚክ የመማሪያ ጥቁር ሰሌዳወዎችን ከግድግዳው ከራሱ በኮንክሪት የበሩን መግቢያ ኮለኖች ከፍተኛ ጥራት ባለው በክሊንከን የመግቢያ ገላጭ ጽሁፍ መባይካ፡፡

የግንባታው ሂደት በከፊሉ በፎቶ ሲገለጽ


በግንባታ ሂደቱ ላይ የወረዳውና የህብረተሰቡ ተሳትፎ የላቀ ነበር ከተወሰኑት በፎቶ


በአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ የተሰራው ግንባታው አሁናዊ ገጽታ


የአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ ያከናወናቸው ተጨማሪ በጎ ተግባራት

 በአሊቾ ው/ወረዳ በቡኔ ቀበሌ በተከሰተው እሳት አደጋ ለተጎዱ ወገኖቻችን የተደረገ ድጋፍ

 30 ኩንታል ዱቄት

 ሩዝ እና

 26 የምግብ ዘይት

 14 ጣቃ የተለያዩ አልባሳት

 230 የቤት መስሪያ ቆርቆሮ

 22 ፓኬት ሚስማር

 በመለገስ ወገናዊ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡

የአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ ያከናወናቸው ተጨማሪ በጎ ተግባራት ከተወሰኑት በፎቶ


አገታ ኤጀሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ የችግኝ ተከላ

 የአገታ ኤጀሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ ሀገራዊ ጥሪን በመቀበል አረንጓዴ አሻራውን አኑሯል

 100 ረጅሙ ፓይነስ ጽድ

 40 አጭሩ ፓይነስ ጽድ

 20 ዝግባ

 20 ወይራ

 40 ዘንባባ

 10 ሸውሸዌ

 10 ሩማን

 20 ማንጎ

 በድምሩ ከ260 በላይ ችግኞች ተተክለዋል

አገታ ኤጀሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ የችግኝ ተከላ በፎቶ ሲገለጽ


በመጨረሻም

 እቅዳችን ብዙ ነው

 ተባብረን ከሰራን ከወረዳች እና ከዞናችን አልፎ ለመላው ሀገራችን የሚተርፉ መልካም ስራዎችን መስራት እንችላለን

’’በባድ ዡቦ በሜልቾ ሬር ኢቀራን አኒርን’’ሀጂ አህመዲን ሀጂ ረዲ

© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved