ከላይ መግቢያው ላይ እንደተገለፀው ፅ/ቤቱ በአ/ው/ወ/አስተዳደር ውስጥ ካሉ 32 ሴክተሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን በአሁን ወክት በወረዳው አስተዳደር አዲሱ ህንፃ ውስጥ መቀመጫውን በቢሮ ቁጥር 31፣32 እና 33 በማድረግ ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ፅ/ቤቱ መጀመሪያ አንድ የስራ ሂደት የነበረው በአሁን ወክት በሶስት ዋናዋና ዳይሬክቶሬቶች እና በሁለት የደጋፊ የስራ ሂደቶች ተዋቅሮ ይገኛል፡፡ሶስቱ ዋናዋና ዳይሬክቶሬቶች አኮቴ ዳይሬክቶሬት፣የሶፍትዌርና ድረ-ገጽ ዳይሬክቶሬት፣የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ሲሆኑ ሁለቱ ደጋፊ የስራ ሂደቶች ደግሞ የሰው ሀብትና የልማት ዕቅድ ናቸው፡፡ ፅ/ቤቱ መጀመሪያ ሲቋቋም አንድ (01)ባለሙያ ና አንድ (01)ሀላፊ በድምሩ ሁለት (02) ባለሙያ የነበሩት ሲሆን በአሁን ወክት በዋናዋና የስራ ሂደቶች አምስት (05)ባለሙያ፣ በደጋፊ የስራ ሂደቶች ደግሞ ሁለት (02) ባለሙያ እና አንድ ሀላፊ በድምሩ ስምንት(08) ባለሙያ ይዟል፡፡
2. የሴክተሩ ባለድርሻ አካላት የነበሩ ዋና ዋና ችግሮች
በሴክተሩ ባለድርሻ አካለት ከነበሩ ዋናዋና ችግሮች መካከል፡-
ለሴክተሩ የነበራቸው አመለካከት አነስተኛ መሆኑ
የሴክተሩ መቋቋም ለወረዳው ምንም ጥቅም ዬለውም ብለው ማሰባቸው
ሴክተሩ የተቋቋመበትን ኣላማ አለመገንዘባቸው
የሴክተሩን የህዝብ ክንፍ ለይተው አለማስቀመጠቸው እና የመሳሰሉት ዋናዋና ችግሮች ነበሩ፡፡
2.1 በአመራሩ በኩል የነበሩ ጉድለቶች
ለሴክተሩ የነበራቸው ግምት ዝቅተኛ መሆኑ
አብሮ የመስራት ፍላጎት አለመኖሩ
ችግሮችን የጋራ ለማድረግ የነበረው ፍላጎት ዝቅተኛ መሆኑ እና የመሳሰሉት ነበሩ፡፡
ተገቢውን እንቅስቃሴ አለማድረጉ
ለሴክተሩ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ላሟሟለት የነበረው እንቅስቃሴ ዝቅተኛ መሆኑ
ሴክተሩ ሲቋቋም ተገቢ የሆነ ግንዛቤ አለመውሰዱ
ከሴክተሩ አላማ ጋር ተገቢ የሆነ ግንዛቤ ልምድ አለመኖሩ እና የመሳሰሉት ጉድለቶች ነበሩ፡፡
ለስራው ተነሳሽነት አለማሳየት
ሰዓትን በአግባቡ አለመጠቀም
የኔነት ስሜት አለመኖር
የመቀናጀት ችግር እና የመሳሰሉት ጉድለቶች ነበሩ፡፡
የባለሙያ እጥረት መኖሩ
ለባለሙያዎች ልዩ የሆነ ጥቅማጥቅም አለመኖሩ<
ለስራ ሂደቱ ተገቢ የሆነ ሰው አለመመደቡ
ለስራው የሚሆኑ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን አለሟሟላቱ
ምቹ የሆነ የስራ ቦታ አለማመቻቸቱ
ባለሙያውች ያለባቸውን ችግር መቅረፍ እንዳለባቸው ውይይት ተደረገ
ማን ምን መስራት እንዳለበት/የስራ ክፍፍል ተደረገ
የመግቢያ እና መውጫ ሰዓት እዲስተካከል ተደረገ
ከዞን ለድጋፋ ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የስራ አቅጣጫ እንዲወሰድ ተደረገ
ከወረዳው ፐ/ሰ እና ሰው ሀብት ቢሮ በሚመጡ ባለሙያዎች ድጋፍ እንዲደረግ ተደረገ
የህዝብ ክንፍ አካላት ተለይተው እንዲታወቁ ተደረገ
ሴክተሩ ከመቋቋሙ በፊት ሁሉም ሴክተር በሚባል ደረጃ ለኢኮቴ መሳሪያዎች አያያዝና አጠቃቀም የነበረው ግንዛቤ አነስተኛ የነበረበት ሁኔታ ነበር የነበራው፡፡ ለአብነት ያክል ሴክተሩ ከመቋቋሙ በፊት የኢኮቴ መሳሪያዎች ብልሽት ሲገጥማቸው መልሰው አገልግሎት እንዳይሰጡ ተደርጎ የማከማቸት ስራ ይሰራ ነበር፡፡
ሴክተሩ መጀመሪያ በዘፈቀደ ያደራጅ የነበረውን መረጃ ተሞክሮዎችን በመውሰድ መረጃዎችን በዘመናዊ መልክ ማደራጀት ችሏል፡፡
ሴክተሩ የተዋቀረው በሶስት ዋናዋና የስራ ሂደቶችና በሁለት የስራ ሂዳቶች እነደሆነ ይታወቃል፡፡ ለአብነት በእነዚህ የስራ ሂደቶች የተሰሩ ስራዎችን እንመልከት፡-
በተለያዩ ሴክተሮች የተበላሹ ኮምፒውተሮችን፣ላፕቶፖችን እና ፕሪንተሮችን ተበላሽተው ከተቀመጡበት አሰባስቦ በማምጣት በማምጣት በራሳችን የሚጠገኑትን ራሳችን በመጠገን ከእኛ በላይ የሆኑትን ዳግሞ ሌላ ባለሙያ በማምጣት ከእኛ ባለሙያ አንድ ላይ በመሆን የማስጠገን ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡በዚህም ከወረዳው ይወጣ የነበረ ብዙ ወጪ ማስቀረት ተችሏል፡፡ይህም በብር ሲተመን እስከ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር ወጪ ማዳን ተችሏል፡፡
የሶፍት-ዌር ድረ-ገፅ ልማት ዳይሬክቶሬት window,Microsoft office,ተለያዩ redar, Anti vires መጫንና update ማድረግ በዋናነት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ናቸው፡፡እነዚህን ስራዎች በመስራት ከወረዳው ይወጣ የነበረ 100,000(አንድ መቶ ሺህ) ብር ማዳን ተችሏል፡፡እንዲሁም ከወረዳው ባህልና ቲሪዝም ሴክተር ጋር በመሆን የወረዳችንን ታሪክና የቱሪሰት ቦታዎችን የሚያስተዋውቅ alichotourism.com የሚል ድረ-ገፅ ማልማት ተችሏል፡፡ለዚህም በግል ይሰራ ቢባል እስከ 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ብር ማስቀረት ተችሏል፡፡
የሳይንስና ፈጠራ ስረዎች ዳይሬክቶሬት በየ ት/ት ቤቶች ላይ የፈጠራ ክበባትን ማዋቀርለነሱም ድጋፈ ማድረግ፣አዳዲሰ የተሰሩ የፈጠራ ስራዎችን ማበረታታት፣ለሚሰሩ ግለሰቦች የምክር፣የቁሳቁስና የቴክኒክ ድጋፎችን ማድረግ፣ለተሰሩ ስራዎች አዲስነታቸው ተረጋግጦ የአእምሮዊ ንብረት ባለቤትነት እንዲሰጣቸው ማድረግ እና የመሳሰሉት ስራዎች በዋናነት የሚሰሩ ስራዎች ናቸው፡፡በዚህም መሰረት ለአንድ የፈጠራ ስራ ለሚሰራ ግለሰብ በብር 250(ሁለት መቶ ሀምሳ)ብር ድጋፍ ተበርክቷል፡፡እንዲሁም ዘንድሮ እንደ ሴክተራችን ለመጀመሪያ ግዜ ከአ/ው/ወ/ት/ት/ፅ/ቤት ጋር በመሆን የፈጠራ ስራዎች ኤግዝቢሽንና ባዛር እና ለፈጠራ ስራ ሰሪዎች እንደየስራቸው የማበረታቻ ሽልማት ማበርከት ተችሏል፡፡
© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved 2.2 . በሴክተሩ ሃላፊ በኩል የነበሩ ጉድለቶች
2.3. በሴክተሩ ባለሙያዎች በኩል የነበሩ ጉድለቶች
3. በሴክተሩ ውስጥ የነበሩ ዋና ዋና ችግሮች
4. ችግሮችን ለመፍታት ምን ተደረገ
5. ሴክተሩ ከመቋቋሙ በፊት የኢኮቴ መሳሪያዎች አያያዝና አጠቃቀም
ለአብነት የተቀመጠ ፎቶ

6. የሴክተሩ የመረጃ አያያዝ
የመረጃ አቀማመጥ በፎቶ

የመስክ ፎርማቶች አቀማመጥ

7. ሴክተሩ ከተመሰረተ ጀምሮ የተሰሩ ስራዎች
7.1 በኢኮቴ የስራ ሂደቶች የተሰሩ ስራዎች
በራሳችን ባለሙያ የኮምፒውተር ጥገና ሲደረግ በፎቶ

ከሌላ ቦታ ከመጡ ባለሙያዎች እና ከእኛ ባለሙያ ጋር በመሆን የኮምፒውተር ጥገና ሲደረግ በፎቶ

7.2 በሶፍት-ዌር ድረገፅ ልማት ዳይሬክቶሬት የተሰሩ ስራዎች
በሴክተሩ ባለሙያዎች የተሰራ ድረ-ገፅ ከፔጁ ለይ የተወሰኑት በፎቶ


7.3 በሳይንስና ፈጠራ ስረዎች ዳይሬክቶሬት የተሰሩ ስራዎች
በፈጠራ ስረዎች ዳይሬክቶሬት የተሰሩ ስራዎች በፎቶ ሲገለጽ

